WWC Check ምንድ ነው?

የ Working with Children Check (ማጣሪያ) ማካሄድ የሚረዳው ህጻናትን ከወሲባዊና አካል ጉዳት ለመከላከል ሲሆን ይህም ከእነሱ ጋር ለሚሰሩ ወይም እንክብካቤ በሚሰጡ ሰዎች ላይ የማጣራት ሂደት በማካሄድ ችግሩ እንዳይፈጠር ለማረጋገጥ ይሆናል።

ማጣሪያ ማድረግ የሚያስፈልገው ማን ነው?

Worker Screening Act 2020 (አንቀጽ ህግ) መሰረት ከዚህ በታች ላሉት ከህጻን ጋር በተዛመደ ስራ አምስት ሁኔታዎች በሙሉ ካሟሉ ያጣሩ:

  1. እድሜያቸው ከ 18 ዓመት በታች ከሆኑ ህጻናት ጋር አብረው በፈቃደኝነት ወይም በክፍያ ሥራ ለማካሄድ እርስዎ ጐልማሳ የመሆን
  2. በአንቀጽ ህጉ/Act ላይ (‘በሙያ መስኮች’ ተብሎ በሚጠራው) መሰረት ከተዘረዘሩት ውስጥ በአንደኛው አገልግሎትቶች፤ ቦታዎች ወይም አካላት ውስጥ ከህጻናት ጋር እየሰሩ ከሆነ ነው
  3. የርስዎ ሥራ በአብዛኛው ከህጻናት ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ ሲሆን ይህም ፊት ለፊት በአካል፤ በጽሁፍ፤ በንግግር እና በኤሌትሮኒክስ ግንኙነትን ያካትታል
  4. ከህጻናት መገናኘቱ ከርስዎ የሥራ ድርሻ አንዱ አካል እንደሆነና ለርስዎ ሥራ በድንገት የሚፈጠር አይደለም
  5. በአንቀጽ ህግ/Act** መሰረት ከማጣሪያ መውሰማካሄድ ነጻ አይሆኑም።

**ዝርዝር መረጃ ከህጻናት ጋር ስለመሥራት/Working with Children በሚለው ድረገጽ ላይ ይገኛል።

በመጀመሪያ የማጣሪያ ማመልከቻ ሳያስገቡ ከህጻናት ጋር በተዛመደ መስራቱ ወንጀል መፈጸም ይሆናል።

እንዲሁም የርስዎ ድርጅት ለማጣሪያ ማመልከቻ ከማስገባትዎ በፊት ከህጻናት ጋር በተዛመደ ስራ እንዲጀምሩ ከጠየቁ ወንጀል ነው።

እንዴት ማመልከት እችላለሁ?

  • ማጣሪያ በሚለው ድረገጽ መግባትና በቪክቶሪያ ውስጥ ማመልከት/Apply in Victoria (External link) ወይም ከአስተዳደር ግዛት ውጭ ሆኖ ማመልከት/Apply from interstate የሚለውን መምረጥ
  • በመስመር ላይ የማመልከቻ ቅጽ መሙላት፤ ስለርስዎ ዝርዝር መረጃ ማቅረብ እና ከህጻን ጋር በተዛመደ ስራ በየትኛው ድርጅት ስለሚያካሂዱ
  • የቪክቶሪያ አመልካቾች ማንነታቸውን በመስመር ላይ መግለጽ ይችላሉ። ከአስተዳደር ግዛት ውጭ የማመልከቻ መረጃ ወረቀት ላይ የሚገለጸው ከአስተዳደር ግዛት ውጭ በሚቀርቡ ማመልከቻዎች ላይ እንዴት የነሱን ማንነት መግለጽ እንደሚችልና የእነሱን ማመልከቻ እንዴት ማስገባት እንደሚችሉ ነው
  • የቪክቶሪያ አመልካቾች ያላቸውን ማመልከቻ የሚያጠናቅቁት በ Australia Post ማውጫ ላይ ተሳታፊ ለመሆን በኢሜል ተደርጐ በኮምፒተር የሚነበብ ኮድ እና መመሪያዎች እንዲጠቀሙ ይላክላቸዋል።

በፈቃደኝነት ሥራ ማጣሪያን ከህጻን ክፍያ ጋር ለተዛመደ ሥራ መጠቀም ወንጀል ሲሆን - ክፍያ ለሚካሄድበት ሥራ የተቀጣሪን ማጣሪያ መጠቀም አለበት።

ማጣሪያው በሚካሄድበት ጊዜ መስራት እችላለሁን?

አንቀጽ ህጉ/Act የሚፈቅደው ብዙዎች ሰዎች የማጣሪያ ሥራ ሂደት በሚደረግበት ጊዜ ከህጻን ጋር የተዛመደ ሥራ እንዲያካሂዱ ይህም ተግባራዊ የሚሆነው የማጣሪያ ማመልከቻው ከገባ በኋላ ነው። ይሁን እንጂ በህጉ መሰረት ከዚህ በታች ያሉት ካለብዎት መሥራት አይችሉም:

  • በአንቀጽ ህግ/Act ክፍል 2 መርሃ ግብር/Schedule 5 በተዘረዘረው ለወሲብ፤ ለሁከት ፈጠራ ወይም ለአደንዛዥ እጽ ጥፋት ወንጀል ፍጻሜ ክስ ወይም ጥፋተኛ ሆኖ ለተገኘ
  • ከህጻናት ጋር ስለመሥራት ህግ በተዛመደ እንዳይሰሩ ታግደዋል
  • ለ WWC ያላካተተ ከተሰጠና በተከታታይ ማጣሪያውን አለማለፍ
  • በህጻን ቀጣሪና ተቀጣሪ አንቀጽ ህግ/Child Employment Act 2003 . መሰረት ሲቀጠሩ በህጻን ላይ ቁጥጥር ይደረግብዎታል
  • በህጻናት አገልግሎት አንቀጽ ህግ/Childrens Services Act 2020 ዓ.ም ወይም በ Education and Care Services National Law 2010 (አንቀጽ ህግ) (ቪክቶሪያ) በሚተዳደር አገልግሎት ውስጥ ስለመስራት
  • ለሚከተለው ከተጋለጡ:
    • በወሲባዊ ጥፋተኛ ምዝገባ አንቀጽ ህግ/Sex Offenders Registration Act 2004መሰረት ሪፖርት የማድረግ ግዲታ ስለመኖር
    • የመቆጣጠር ትእዛዝ ወይም የእስር ቤት ትእዛዝ ካለ ነው።

ማጣሪያው በሚካሄድበት ጊዜ ስለመስራት ለርስዎ ድርጅት መጠየቅ፤ ይህም አንዳንድ ድርጅቶች ለአመልካቾች እንዲሰሩ የሚፈቅዱላቸው የማጣሪያ ፈተናውን ካለፉ በኋላ ብቻ ስለሆነ ነው።

ምንድ ነው የሚጣራው?

ማጣሪያ የሚደረግልዎት ለወሲባዊ፤ ሁከት ፈጠራና ለአደንዛዥ እጽ ወንጀል ፍጻሜ እና በድርጅቱ አንቀጽ ህግ በተዘረዘሩት ጠቃሚ ለሆኑ የዲስፒሊን ወይም በደንቦች ላይ ጥሰት ካለ ነው። ዝርዝር ወንጀሎች/list of offences (External link) በእኛ ድረገጽ ላይ ይገኛል።

በአንቀጽ ህግ/Act መሰረት የተካሄደ ማንኛውም ውሳኔ ላይ ህጻናትን ከወሲባዊ ወይም ከአካል ጉዳት መከለከሉ ዋናው ግምት ውስጥ የሚገባ ይሆናል።

የ WWC Check ማጣሪያ ስለማለፌ እንዴት አውቃለሁ?

የማጣሪያውን ካለፉ ለርስዎም ሆነ ለርስዎ ድርጅት እናሳውቃለን።

ማጣሪያውን ካላነሳነው ወይም እርስዎ ካልመለሱት ለአምስት ዓመታት ተግባራዊ ይሆናል።

ከህጻን ጋር በተዛመደ ሥራ ለመቀጠል ከፈለጉ የርስዎን ማጣሪያ ለማሳደስ ጊዜው ከማለቁ በፊት በ6 ወራት ውስጥ እና ጊዜው ከተቃጠለ በኋላ በ3 ወራት ውስጥ ማመልከት አለብዎት።

 

Image

የወንጀል ምዝገባ ሪኮርድ ወይም ጠቃሚ የሆነ የዲሲፕሊን ስርአት ወይም የደንብ መጣስ ሪኮርድ ካለብኝስ ምን ይደረጋል?

ሁሉም ጠቃሚ ለሆኑ የድሲፕሊን ስርአት ወይም የመደባዊ ህግ መጣስ አይደለም ሲባል በአንቀጽ ህጉ መሰረት ለህጻናት ህጋዊ ባልሆነ ደህንነት ችግር ውስጥ ታስገባለህ ማለት ነው።

የማጣሪያ ፈተናውን ቢያልፉም ወይም ባያልፉም እንደ አንጻራዊ የሙያ ተግባር ዓይነት ሲሆን ይህም በፈጸሙት ወንጀል እና በነዚህ ጉዳዮች ላይ ባሉት ሁነታዎች ተመርኩዞ ይሆናል።

ለማጣሪያ ህገ-ወጥ ማመልከቻ የሚሆነው እርስዎ:

  • በወሲባዊ ጥፋተኞች ምዝገባ አንቀጽ ህግ/Sex Offenders Registration Act 2004 መሰረት ለተራዘመ ቁጥጥር ትእዛዝ ወይም ውስጣዊ የሆነ የተራዘመ ቁጥጥር ትእዛዝ ላለበት
  • የእስር ቤት ትእዛዝ ወይም የመቆጣጠር ትእዛዝ ላለበት ነው።

ስለ ግላዊ ሁኔታዎ የሚያማክርዎ ገለልተኛ የሆነ የህግ አማካሪ ያስፈልግዎታል።

የ Check ማጣሪያ መመዘኛ ካላለፍኩስ ምን ይደረጋል?

ለህጻናት በማይገባ ችግር ውስጥ የሚያስገቡ እንደሆነ ካመንበት፤ እርስዎ ከህጻን ጋር በተዛመደ መስራት እንደታገዱ እንደፈለግን ጊዚያዊ ከ WWC መወገጃ በማቅረብ እናሳውቃለን። ይህ ለእኛ እንዲጽፉልን እድል እንደሚሰጥዎና ታዲያ የማጣሪያ ፈተናውን ለምን ማለፍ እንዳለብዎት ያሳስብዎታል።

የርስዎን ምክንያት ግምት ውስጥ ከገባ በኋላ በማጣሪያው ከወደቁ፤ ከህጻን ጋር በተዛመደ መስራት እንደታገዱ የ WWC መወገጃ በመስጠት እናሳውቃለን።

ሁኔታዎች ላይ ከታገቱ፤ ለ WWC መወገጃ በሰጠነው ውሳኔ ላይ በ28 ቀናት ውስጥ አቤቱታ ለቪክቶሪያ ሲቪልና አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት (VCAT) ማመልከት ይችላሉ።

የእኔ ግላዊነት እንዴት ይጠበቃል?

በግላዊነትና ሚስጢራዊነ ህጎች የተሳሰርን ነን። እኛ እንዴት ግላዊ መረጃን መውሰድና መጠቀም እንዳለብን የ Worker Screening Act 2020, Privacy and Data Protection Act 2014 እንዲሁም Health Records Act 2001 (አንቀጽ ህግ) ቁጥጥር ያደርጋል።

ስለርስዎ ማመልከቻ ማንኛውንም ጊዜያዊ ወይም የመጨረሻ ውሳኔ ለርስዎ ድርጅት/ቶች እናሳውቃለን ታዲያ የርስዎ ማጣሪያ ታግዶ፤ ተቀይሮ ወይም ተነስቶ ከሆነ ወይም ያቀረቡትን ማመልከቻ አቁመውት ከሆነ። ከርስዎ ሪኮርድ የሆነን ድርጅት ካወጡ፤ ታዲያ ለነዚህ ድርጅቶች ከሪኮርድ እንዳወጧቸው እናሳውቃለን። ላለዎት ወንጀል ነክ ፍጻሜ ወይም የዲስፕሊን ስርአት ጕድለት ሪኮርድ ዝርዝር መረጃ ለድርጅትዎ አናቀርብም።

የ WWC Check ማጣሪያ እንደ ፖሊስ ማጣሪያ ተመሳሳይ ነውን?

አይደለም፡ በ Working with Children Check የሚጣራው የርስዎን ወንጀል ፍጻሜ ወይም የዲስፕሊን ስርአት ወይም ደንቦች ላይ ጥሰት ሪኮርድ እና በህይወት ዘመንህ ጠቃሚ ለሆነ የወሲባዊ፤ ሁከት ወይም የአደንዛዥ እጽ ወንጀል ስለመፈጸሙ ጠንከር ያለ ግምገማ ያደርጋል። በተወሰነ የጊዜ ገደብ የ Police Check ዝርዝር ወንጀሎችን ያቀርባል።

የ Working with Children Check ተቆጣጣሪ ካርድ ለያዙት በካርድ ህይወት ዘመናቸው ላይ ወንጀልና የዲስፕሊን ስርአት ወይም በደንቦች ጥሰት ላይ ሪኮርድ ካላቸው ያጣራል። በሁለቱ የሚደረገው ማጣሪያ በጣም የተለያየ በመሆኑ አንዳንድ ድርጅቶች ሁለቱንም ማጣሪያዎች ይፈልጋሉ።

በበለጠ ዝርዝር መረጃ በ በተለያዩ ማጣሪያዎች ያለውን ልዩነት በ Working with Children ድረገጽ ላይ ‘ፖሊስ ማጣሪያ/Police Checks (External link)’ በሚለው ስር ቀርቧል።

ለበለጠ መረጃ

በድረገፅ

www.workingwithchildren.vic.gov.au (External link)

በኢሜል
workingwithchildren@justice.vic.gov.au (External link)

ለደንበኛ ድጋፍ ቡድን በስልክ
1300 652 879

ሰዓት ከጥዋቱ 8.30am እስከ ከሰዓት በኋላ 5.00pm፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ (ህዝባዊ በዓላት ካልሆኑ በስተቀር)

መስማት ለተሳነው የተለፎን አገልግሎት (TTY)
13 36 77

መናገር እና ማዳመጥ
1300 555 727

አስተርጓሚ ከፈለጉ፤ እባክዎ ለ Translating and Interpreting Service በስልክ 13 14 50 ይደውሉና ከ Working with Children ደንበኛ ድጋፍ አገልግሎት መስመር ጋር እንዲያገናኝዎት መጠየቅ።

ትልቅ ህትመት
በኢሜል workingwithchildren@justice.vic.gov.au (External link)

ይህ መረጃ ለአጠቃላይ መመሪያ ብቻ ተብሎ የወጣ ነው። እንደ ህጋዊ የሆነ ምክር ተብሎ የተሰጠ እንዳልሆነ እና በዚህ ላይ ብዙም መመካት አይገባም። በርስዎ ላይ ስላለ የተለየ ሁኔታዎች ላይ ጠቃሚ የሆነ ህጋዊ ምክር ማግኘቱ ይመረጣል።